ተግባራቶቻችን
አምስቱ ዋና ዋና ተግባራቶቻችን — በፍቅር፣ በወገንተኝነት እና በቀጣይነት።
1 / 5
የበዓል መዋያ ስጦታዎች
ማህበራችን በአሁኑ ሰዓት በዓመት አራት ጊዜ — አዲስ ዓመት፣ ገና፣ ረመዳን እና ፋሲካ — በጠቅላላው ወደ 80 ለሚጠጉ ወገኖች የበዓል መዋያ ስጦታ ያበረክታል። እያንዳንዱ የበዓል ስጦታ ዶሮ፣ 3 ኪ.ግ ሽንኩርት፣ 1–2 ሊትር ዘይት፣ 1/2 ኪ.ግ በርበሬ እና 10 እንቁላል ይይዛል።



2 / 5
እናስተምራቸው
ዋነኛው ዓላማ የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ልጆች የሆኑ ነገር ግን የራሳቸው የነገ ብሩህ ተስፋ ያላቸውን ታዳጊዎች በመማሪያ ቁሳቁስ እና በሃሳብ ስንቅ መደገፍ ነው። በ2016 ክረምት 50 ለሚሆኑ ታዳጊዎች 1 ደርዘን ደብተር፣ እስክርቢቶ፣ እርሳስ፣ ላፒስ እና መቅረጫ ማገዝ ችለናል — ከመዋለ ህፃናት እስከ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ደርሰናል።



3 / 5
በፍቅር እናልብሳቸው
«ሁለት ያለው አንዱን ለሌለው ይስጥ» በሚለው የፍቅር ቃል ከራሳችን በመጀመር — ለኛ ትርፍ የሆነውን ነገር ግን ለሌሎች ወሳኝ የሆነውን ልብስ በተለያዩ ወቅቶች ከበጎ ሰጪዎች በማሰባሰብ በርካታ ጎዳና ላይ ላሉ ወገኖቻችን አድርሰናል። ይህ እንቅስቃሴ ድጋፍ ባገኘንበት ጊዜ ሁሉ ይደረጋል።



4 / 5
ለእኔዋ እህቴ
ሴት እህቶችን እና እናቶችን በንፅህና አጠባበቅ ለማገዝ የተጀመረ ነው። በሀገራችን በተለይም በገጠር አካባቢ ለወርሃዊ አበባ ያለውን የግንዛቤ እንዲሁም የንፅህና መጠበቂያ እጥረት በመመልከት — በዘንድሮ ዓመት 30 ለሚሆኑ ሴት ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ከልብስ ሳሙና ጋር እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሰጥተናል።



5 / 5
የቀን ተቀን ስራ
ማህበሩ በቀን ተቀን ተግባሩ ለ4 ሰዎች ቤት ተከራይቷል፤ ለ3 ሰዎች የአስቤዛ ወጪን ይሸፍናል፤ ለ3 ተማሪዎች የትምህርት ወጪን ይሸፍናል፤ ለሁሉም በስሩ ላሉት ወገኖች የጤና ጉዳይ ከማሳከም እስከ መድኃኒት መግዛት ያከናውናል፤ እንዲሁም ለ3 ቤተሰብ ሙሉ የሕክምና መድህን ሽፋን አድርጓል።


