ስለ እኛ

ደጉ ሳምራዊ ጅማሮውን በቢሾፍቱ ከተማ ወጣቶች አድርጎ አሁን ላይ በተለያዩ ከተሞች ያሉ ወጣቶችን በስሩ የያዘ የበጎ አድራጎት ማህበር ነው።

ታሪካችን

ማህበሩ ስራውን ሲጀምር ለአቅመ ደካሞች የበዓል መዋያ በመስጠት ነበር። ዛሬ ላይ በዓመት አራት በዓላትን — አዲስ ዓመት፣ ገና፣ ረመዳን እና ፋሲካ — በየበዓሉ ከሃምሳ በላይ አቅመ ደካማ ወገኖችን ለመድረስ ችሏል።

እንዲሁም በየዓመቱ ክረምት ላይ «እናስተምራቸው» በሚል ተነሳሽነት ለአቅመ ደካማ ወላጅ ልጆች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ያደርጋል፤ በቋሚነትም ከቀን ተቀን የሚረዳቸው ወገኖች አሉት።

መርሃችን

«ወጣትነት ለመልካምነት» — ወጣትነት በማህበረሰቡ ዘንድ የሚታወቀው ለማህበረሰቡ ተቆርቋሪ አለኝታ፣ ትኩስ ሀይል እና የወደፊት የሀገሪቱ ተረካቢ መሆኑ ነው። ይህንን በተግባር ለማሳየት እንሰራለን።

ስኬቶቻችን

ማህበራችን ባለፉት አራት ዓመታት ያሳካቸው።

  • ከ10 በላይ በዓላትን በየበዓላቱ ከ80 በላይ ወገኖች የበዓል መዋያ አድርሰናል።

  • ለተከታታይ ሁለት ዓመት ከ50 በላይ ለሆኑ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ አበርክተናል።

  • ጎዳና ላይ ያሉ ወገኖችን የመመገብ እና የማልበስ ስነ ስርዓት አካሂደናል።

  • «ለኔዋ እህቴ» ለ30 እህቶች የንፅህና መጠበቂያ አድርሰናል።

  • ለ4 ሰዎች ቤት ተከራይተናል፤ ለ3 ሰዎች የአስቤዛ ወጪ እንሸፍናለን።

  • ለ3 ቤተሰብ ሙሉ የሕክምና መድህን ሽፋን አድርገናል።

አባል ይሁኑ

በማህበረሰባችን ውስጥ ለአቅመ ደካማ ወገኖች ርህራሄን ወደ ተግባር ከሚቀይር የወጣቶች ማህበር ጋር ይቀላቀሉ።

አባል ይሁኑ