የወጣቶች በጎ አድራጎት ማህበር · ቢሾፍቱ

«ወጣትነት ለመልካምነት»

ደጉ ሳምራዊ አቅመ ደካማ ወገኖችን በበዓል ስጦታ፣ በትምህርት ቁሳቁስ፣ በአልባሳትና በቀን ተቀን ድጋፍ የሚደርስ በህጋዊ መንገድ የተመዘገበ የወጣቶች ማህበር ነው።

ባለፉት አራት ዓመታት

የተከበሩ በዓላት

10+

የተከበሩ በዓላት

በየበዓሉ የተደረሱ ወገኖች

80+

በየበዓሉ የተደረሱ ወገኖች

የመማሪያ ቁሳቁስ የተደገፉ ተማሪዎች

50+

የመማሪያ ቁሳቁስ የተደገፉ ተማሪዎች

የንፅህና መጠበቂያ የደረሳቸው እህቶች

30

የንፅህና መጠበቂያ የደረሳቸው እህቶች

ቤት የተከራየላቸው ወገኖች

4

ቤት የተከራየላቸው ወገኖች

ሙሉ የሕክምና መድህን ያላቸው ቤተሰቦች

3

ሙሉ የሕክምና መድህን ያላቸው ቤተሰቦች

ተግባራቶቻችን

ከበዓል ስጦታ እስከ ቀን ተቀን ድጋፍ — አምስቱ ዋና ዋና ተግባራቶቻችን።

  • የበዓል መዋያ ስጦታዎች

    ማህበራችን በአሁኑ ሰዓት በዓመት አራት ጊዜ — አዲስ ዓመት፣ ገና፣ ረመዳን እና ፋሲካ — በጠቅላላው ወደ 80 ለሚጠጉ ወገኖች የበዓል መዋያ ስጦታ ያበረክታል። እያንዳንዱ የበዓል ስጦታ ዶሮ፣ 3 ኪ.ግ ሽንኩርት፣ 1–2 ሊትር ዘይት፣ 1/2 ኪ.ግ በርበሬ እና 10 እንቁላል ይይዛል።

  • እናስተምራቸው

    ዋነኛው ዓላማ የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ልጆች የሆኑ ነገር ግን የራሳቸው የነገ ብሩህ ተስፋ ያላቸውን ታዳጊዎች በመማሪያ ቁሳቁስ እና በሃሳብ ስንቅ መደገፍ ነው። በ2016 ክረምት 50 ለሚሆኑ ታዳጊዎች 1 ደርዘን ደብተር፣ እስክርቢቶ፣ እርሳስ፣ ላፒስ እና መቅረጫ ማገዝ ችለናል — ከመዋለ ህፃናት እስከ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ደርሰናል።

  • በፍቅር እናልብሳቸው

    «ሁለት ያለው አንዱን ለሌለው ይስጥ» በሚለው የፍቅር ቃል ከራሳችን በመጀመር — ለኛ ትርፍ የሆነውን ነገር ግን ለሌሎች ወሳኝ የሆነውን ልብስ በተለያዩ ወቅቶች ከበጎ ሰጪዎች በማሰባሰብ በርካታ ጎዳና ላይ ላሉ ወገኖቻችን አድርሰናል። ይህ እንቅስቃሴ ድጋፍ ባገኘንበት ጊዜ ሁሉ ይደረጋል።

  • ለእኔዋ እህቴ

    ሴት እህቶችን እና እናቶችን በንፅህና አጠባበቅ ለማገዝ የተጀመረ ነው። በሀገራችን በተለይም በገጠር አካባቢ ለወርሃዊ አበባ ያለውን የግንዛቤ እንዲሁም የንፅህና መጠበቂያ እጥረት በመመልከት — በዘንድሮ ዓመት 30 ለሚሆኑ ሴት ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ከልብስ ሳሙና ጋር እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሰጥተናል።

  • የቀን ተቀን ስራ

    ማህበሩ በቀን ተቀን ተግባሩ ለ4 ሰዎች ቤት ተከራይቷል፤ ለ3 ሰዎች የአስቤዛ ወጪን ይሸፍናል፤ ለ3 ተማሪዎች የትምህርት ወጪን ይሸፍናል፤ ለሁሉም በስሩ ላሉት ወገኖች የጤና ጉዳይ ከማሳከም እስከ መድኃኒት መግዛት ያከናውናል፤ እንዲሁም ለ3 ቤተሰብ ሙሉ የሕክምና መድህን ሽፋን አድርጓል።

አብረውን ይቁሙ

የያዝነው ዓላማ ተግባራዊ እንዲሆን የእርስዎ ድጋፍና ትብብር ወሳኝ ነው። በትንሽም በትልቅም አስተዋጽኦ የአንድ ወገን ሕይወት ይለወጣል።

እንዴት መደገፍ እንደሚችሉ ይወቁ